ለአፍሪካውያን ፀጉር እና ቆዳ የተዘጋጁ ትክክለኛ ተፈጥሯዊ ምርቶች
ምርቶቻችን፣ በሳይንሳዊ ኺደት ላይ በተመሠረቱ ቀመሮች እና ልባዊ የሙያ ፍቅር ከአፍሪካ ምድር በተገኙ እጽዋት እና ንጥረ ነገሮችን ውህደት የተመረቱ እና ለሁሉም ዓይነት አፍሪካዊ ቆዳ የሚሆኑ ናቸው፡፡
የፀጉር እና የቆዳ መጠበቂያ ምርቶች
በኩራት ኢትዮጵያ ውስጥ የተመረተ
ሙሉ በሙሉ ተፈጥሯዊ
ጥላ፣ ምርቶቹን በልዩነት ለማዘጋጀት ከመላው አፍሪካ የሚሰበሰቡ፤ እጅግ ጥራታቸውን የጠበቁ ግብዓቶችንና ሀገር በቀል ንጥረ ነገሮችን ይጠቀማል!
ለእያንዳንዱ የቆዳ ቀለም እና ዓይነት ተስማሚ ሆነው የሚዘጋጁ መዋቢያዎች!
ላንቺ ለውቢቷ!
ምርቶቻችን፣ በልባዊ የሙያ ፍቅር እና በጥንቃቄ፣ በዕጅ የተዘጋጁ ሲሆን በቶሎ የሚቆጣ ቆዳ ላላቸው ደንበኞቻችንም ሁነኛ መፍትሔ እና ተስማሚ ናቸው፡፡

የጥቁር አዝሙድ ዘይት
"በዕድሜ ምክንያት ለሚፈጠር የቆዳ መሸብሸብ ሁነኛ መፍትሔ! በፀረ-አንቲኦክሲደንቶች፣ በአስፈላጊ ፋቲ አሲድ፣ ቫይታሚኖች እና አሚኖ አሲዶች የበለጸገ።"

የሰሊጥ ዘይት
በሌላኛው መጠሪያው ጂንጌሊ ዘይት በመባል የሚታወቅ ሲሆን ቆዳን ከማለስለስ ባሻገር አንጻባራቂ እንዲሆን ያግዛል፡፡ የፀጉርን ጤናማነት በመጠበቅ ረገድም አቻ የለውም!

የአፋር ጨው
የሚያቃጥል እና ቶሎ የሚቆጣን ቆዳን በማከም ቆዳው ለስላሳ እና ጥርት ያለ እንዲሆን የሚያስችልና በማእድናት በልፅጎ የታሸገ! ቆዳ እንዳይደርቅ እና እንዳይቆጣ የሚከላከል! የቆዳ መሳሳትን የሚከላከል!

የፅጌረዳ ውኃ
ላለፉት ብዙ ሺህ ዓመታት ለመዋቢያ አገልግሎት ላይ የዋለ፣ የቆዳን ውበት ይበልጥ በማጎልበት ጉዳቱን የሚቀንስ እና በፀረ-ባክቴሪያ ኃይሉ ብጉርን እና ሽፍታን የሚከላከልና የሚቀንስ!

የአቮካዶ ዘይት
ሁሉንም የቆዳ ዓይነት በሚጠቅሙ ንጥረ ነገሮች ከመበልጸጉ ባሻገር ቫይታሚን ኢ እና ቆዳችን ትክክለኛ ቀለም እንዲኖረው የሚረዱ አስፈላጊ ፋቲ አሲዶችን የያዘ ነው!

ነጭ ማር
በቫይታሚን ኤ እና ቢ፣ ካልሺየም፣ ፖታሲየም፣ ማግኒዥየም፣ ፎስፈረስ እና ዚንክ የበለጸገ እንዲሁም እጅግ ጠቃሚ የሆኑ አንቲ-ኦክሲደንቶችን የያዘ!

ነጭ ማር
በቫይታሚን ኤ እና ቢ፣ ካልሺየም፣ ፖታሲየም፣ ማግኒዥየም፣ ፎስፈረስ እና ዚንክ የበለጸገ እንዲሁም እጅግ ጠቃሚ የሆኑ አንቲ-ኦክሲደንቶችን የያዘ!

ባህር ዛፍ
ይህ ተፈጥሯዊ ግብዓት ለቆዳ፣ ለፀጉር እና ለከንፈር ውበትን በማጎናጸፍ ተወዳዳሪ የለውም! የቆዳ ልስላሴን የሚጠብቁ ሴራሚዶች እና ጠቃሚ ፋቲ አሲዶችን በውስጡ ይዛል፡፡ የቆዳን እርጥበት በማመጣጠን ቆዳችን ፍጹም ለስላሳና አንጸባራቂ እንዲሆን ያስችለዋል፡፡

የካካዋ ቅቤ
ይህ ተፈጥሯዊ ግብዓት፣ በውስጡ በያዛቸው አስፈላጊ ፋቲ አሲዶች ምክንያት ቆዳ ለስላሳ እንዲሆንና እና እርጥበቱ እንደተጠበቀ እንዲቆይ የማስቻል ዐቅም አለው፡፡

የአርጋን ዘይት
"ይህ ተፈጥሯዊ ንጥረ ነገር፣ የቆዳን እና የፀጉርን ልስላሴ ለመጠበቅ ይረዳል፡፡ በውስጡ የያዛቸው ቫይታሚኖች የተጎዳ የቆዳ እና የጸጉር ክፍል በቶሎ እንዲያገግም የሚያስችሉ ሲሆን በፋቲ አሲድና በተለይም ደግሞ በኦሌይሊክ እና ሊኖሌይክ አሲድ የተሞላ ነው።"

የሺኣ ቂቤ
"ይህ ግብዓት፣ ቆዳን እንደገና የሚያድስ፣ ተፈጥሯዊ ወዝን ወደነበረበት የሚመልስ እና የደረቀን ቆዳ በፍጥነት የሚያለሰልስ ነው፡፡ በአስፈላጊ ንጥረ ነገሮች የተሞላ በመሆኑ የተፈጥሮ ቆዳን የሚያጎለብት እና ፈውሱን ከውስጥ ቆዳችን በመጀመር ውበትን የሚያጎናጽፍ ነው፡፡"

ነጭ ማር
በቫይታሚን ኤ እና ቢ፣ ካልሺየም፣ ፖታሲየም፣ ማግኒዥየም፣ ፎስፈረስ እና ዚንክ የበለጸገ እንዲሁም እጅግ ጠቃሚ የሆኑ አንቲ-ኦክሲደንቶችን የያዘ!
ምርቶቻችን
ጥላ፣ በተፈጥሮ ሀብቶች ከታደለው የአፍሪካ ምድር በሚገኙ ግብዓት እና ንጥረ ነገሮች እንዲሁም ማዕድናት በመታገዝ ተፈጥሯዊ የቆዳ እና የፀጉር መንከባከቢያና መዋቢያዎችን ያቀርባል፡፡



ስለውበት መጠበቂያዎች አዳዲስ መረጃዎች በጋዜጣችን በኩል እንዲደርስዎ ይመዝገቡ!
ግዢ በመፈፀም የቅናሻችን ተጠቃሚ ይሁኑ!
ጋዜጣ
የውቦቹ አፍሪካውያን ታሪክ
በልዩነታችን ውስጥ የዳበረውን ውበት ማጉላት
ዋና እሴቶቻችን
"ጥላ፣ የአፍሪካ አህጉር የተፈጥሮ ውበት በሕዝቦቿ ውስጥ እንደሚገኝ ያምናል፡፡ እንደ ኢትዮጵያ ምድር እና ሕዝብ ደግሞ ይህንን እውነታ የሚያረጋግጥ የለም። በቅርሶቿ እና የሰው ልጆች መገኛ በመሆኗ የምትታወቀው ኢትዮጵያ፣ ወደር የለሽ የዘረመል ስብጥርን ተጎናጽፋለች። ይህ በዓይነቱ ልዩ የሆነ የብሔረሰቦች ስብጥር፣ ኢትዮጵያን በአህጉሪቱ ያለውን ማንኛውንም ዓይነት ቀለም የምትወክል፣ የበለጸገች፣ ዘርፈ ብዙ ብሔር ብሔረሰቦችና ባህሎች ባለቤት ያደርጋታል። ኢትዮጵያ ብርቅዬና ምሥጢራዊ ውበት ያላት ሀገር እንደመሆኗ የጥላን ምርቶች እና አፍሪካ ውስጥ ያሉትን የውበት ደረጃዎች በሚገባ መግለጽ ትችላለች።"
ወቅታዊ ዜናዎች
አዲስ እና አጓጊ ዜናዎች
ዘላቂ መፍትሔዎች እና ማኅበረሰባችን
በአፍሪካዊ ባህሎች ላይ የተመረኮዙና የሚኮሩ ምርቶች ባለቤት እንደመሆናችን መጠን ለዘላቂነት እና ማኅበረሰባችንን ለመደገፍ በቁርጠኝነት እንሠራለን።